WHAT WE OFFER

 የምንሰጣቸው ትምህርቶች

የመጽሐፍ ቅዱስ ታላላቅ እውነቶች
መሰረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት (Primary Discipleship Class)

ይህ ክፍል መሰረታዊና ማንኛውም የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ ሊያውቃቸው የሚገቡ እውነቶችን ያካትታል። ስለ ፍጥረት፤ ስለ መለኮት፤ በሰይጣን እና በክርስቶስ መካከል ስለሚደረገው ተጋድሎ፤ ስለ እግዚአብሔር ሕግ፤ ስለ ትንቢትና የጸጋ ስጦታዎች ተማሪዎች በስፋት ይማሩበታል። በየሳምቱ የማስታዎሻ ፈተና የሚሰጥ ሲሆን ትምህርቱን ተምረው ለሚያጠናቅቁ የምስርክ ወረቀት እንዲሁም ጌታን ተቀብለው በዚህ እውነት መጠመቅ ለሚፈልጉ እድሉ ተዘጋጅቷል። 

የትንቢተ ዳንኤልና የዮሐንስ ራእይ ትምህርቶች (Advanced Class)

በዚህ ክፍል ተማሪዎች የትንቢተ ዳን ኤልን እና የዮሐንስ ራእይን መጻሕፍት በጥልቀት ይማራሉ። ይህ ትምህርት ስለ አለም ታሪክ፤ ስለ ተለያዩ ነገሥታት፤ ስለ ሃይማኖታዊ ክህደቶች፤ ስለመጨረሻው ፈተና እንዲሁም የክርስቶስ ዳግም ምጻት በሰፊው ያካትታል። በዚህ ክፍል ተመዝግቦ ለመማር የመሰረታዊውን ትምህርት መማር  ያስፈልጋል።