“ህግህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴ ብርሃን ነው”
መዝሙር 119:105
መግቢያ
መጽሐፍ ቅዱስ “የአምላክ መንገድ ፍጹም ነው፡ የእግዚአብሔር ቃል የነጠረ ነው፤ በእርሱ ለሚታመኑት ጋሻ ነው” በማለት የእግዚአብሔርን ቃል ተጽእኖ ያጎላል። ይህን ታሳቢ በማድረግ ትምህርት ቤታችን ለእግዚአብሔር ቃል ልዩ ፍቅር ባላቸው ወንድሞችና እህቶች ተቋቁሟል። የዚህ ትምህርት ቤት አላማ መሰረታዊ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን በማስተማር ሰዎችን የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር በማድረግ ለዘላለም ሕይወት ማዘጋጀትና መልካምና በጎ ተጽእኖ ፈጣሪ ዜጎች ማድረግ ነው።
በዚህ ድረ ገጽ ውስጥ ተከታታይ የሆኑ መሰረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮዎችን በመማር የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ከመሆን ባሻገር ለዘላለም ሕይወት የሚያዘጋጁና መልካምና በጎ ተጽእኖ ፈጣሪ ዜጋ የሚያደርጉ አስገራሚ ትምህርቶችን ያገኛሉ።
OUR COURSES
የምንሰጣቸው ትምህርቶች