WHO WE ARE

ስለ ትምህርት ቤታችን

የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር የደቀ መዝሙርነት ትምህርት ቤት በተለያየ የሕይወት እርምጃ ውስጥ ያሉና የተለያየ እምነት ያላቸውን ተማሪዎች ተቀብሎ በምስክር ወረቀት ደረጃ ለ4 ወራት የሚዘልቁ ሁለት አይነት ትምህርቶችን ያስተምራል። የመጀመሪያውና ተማሪዎች የሚማሩት  የመሰረታዊ (Descipleship class)  ደቀ መዝሙርነት ትምህርት ሲሆን መሰረታዊና ወሳኝ የሆኑ መጽሐ ቅዱሳዊ እውነቶችን የምናስተምርነት ክፍል ነው። ሁለተኛው ጥልቅና ቀጣይ የሆነ (Advanced Class) ክፍል ሲሆን በዳንኤልና በዮሐንስ ራእይ መጻሕፍት ላይ ትኩረት የሚያደርግ ክፍል ነው። ሁለተኛውን ክፍል ለመማር የመሰረታዊውን ትምህርት ማጠናቀቅ ያስፈልጋል።  

ትምህርቶቹን ተምረው ለሚያጠናቅቁ የምረቃ ስነ ስርዓት ይደረጋል። ጌታን አምነው በጥምቀት ለወንጌል አገልግሎት የእኛን ቡድን እንዲሁም የአድቬንቲስት ቤተክርስትያንን  መቀላቀል ለሚፈልጉ ሁሉ የተለየ መርሃ ግብር ይዘጋጃል። 

የእግዚአብሔር ቃል ለሰው ሁለንተናዊ እድገትና ብልጽግና ወሳኝ ነው። ልብን ክፍት አድርገው በጽሎት ሆነው ሲያጠኑት የግለሰብን፤ የቤተሰብን፤ የሕብረተሰን እንዲሁን የአገርን ገጽታ ያሻሽላል፤ ይቀይራል፤ ይለውጣል። አብረውን በማጥናት የዚህ በረከት ተካፋይ ይሁኑ! 

2019

የምስረታ አመት

28

ትምህርቶች

30

የትምህርት ቤቱ አስተዳዳሪዎችና አስተማሪዎች